ግብፅ ለየብስ ሀገራት ወታደራዊ የባሕር መግቢያ እንደማትፈቅድ አስታወቀች
የንግድ መግቢያ ብትፈቅድም፡ የቀይ ባሕር ወታደራዊ መግቢያን ከልክላለች።

ግብፅ በባሕር ዳርቻ ካሉ ሀገራት ጋር በሚደረግ ስምምነት የንግድ መግቢያ ስትፈቅድ፡ ለየብስ ሀገራት ግን የቀይ ባሕር ወታደራዊ መግቢያ መከልከሏን አስታውቃለች።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድር አብደልዓጢ ይህን በመግለጽ፡ በቀጣናው የባሕር ደህንነትን ለማጠናከር ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር የሚደረገው ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ውሳኔው የመጣው ኢትዮጵያ የባሕር መግቢያ ለማግኘት የምታደርገው ጥረት በቀንደ አፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ አዳዲስ ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን ባስነሳበት ወቅት ነው።
ግብፅ የንግድ መስመሮችን ብትፈቅድም፡ ወታደራዊ እንቅስቃሴን መከልከሏ በቀጣናው ያላትን ስትራቴጂያዊ ተፅዕኖ ለማስጠበቅ ያለመ መሆኑ ይገለጻል።
