የድሮን ጥቃቶች ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ቀጥለዋል
በገርሁ ስርናይና በኢሮብ ትምህርት ቤቶች ተመትተዋል፤ በካፍታ ሽራሮ ሰፊ ቃጠሎ ቀጥሏል

የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እሑድ ጥቅምት 11 ከሰዓት በፊት ሌላ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ማድረሱ ተገልጿል።
ወታደራዊ በረራዎችንና የድሮን ጥቃቶችን የሚከታተለው ጸሐፊ ሪች ቴድ፡ በሰሜን ትግራይ ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ በገርሁ ስርናይ የሚገኘው የእገላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኢላማ መሆኑን አስታውቋል፤ ከጥቃቱ በኋላ ከትምህርት ቤቱ ጥቁር ጭስ የሚያሳይ ምስልም አጋርቷል።
በተመሳሳይ፡ በኢሮብ አስተዳደር የሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተከታታይ ሦስት ጊዜ ተመትቶ ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል መውደሙና በርካታ ሲቪሎች መሞታቸው ይገለጻል።
የአሜሪካው ናሳ ፊርምስ፡ በኢሮብና በራማ አካባቢ በርካታ የሙቀት ምልክቶችን መለየቱን አረጋግጧል። በካፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክም ሰፊ ቃጠሎ ቀጥሏል።
