ቻይና ለሰሜን ኢትዮጵያ ሁኔታ አራት መርሆዎችን አቀረበች
ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፡ የአፍሪካ መሪነት፡ ሉዓላዊነት፡ ግጭት ማቆምና መሠረታዊ ምክንያት መለየትን ጠቅሰዋል።

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ፡ ጥቅምት 19 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፡ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በአፍሪካ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ለመፍታት አራት መርሆዎችን ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
የመጀመሪያው መርህ ለአፍሪካ መሪነት ቅድሚያ መስጠት ሲሆን፡ የአፍሪካ ሕዝብ የአህጉሩ እውነተኛ ባለቤት እንደመሆኑ በቀጣናዊ ጉዳዮች ማዕከላዊ ሚና ሊጫወት እንደሚገባ ይገልጻል።
ሁለተኛው፡ ሁሉም ወገኖች የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር ዓላማዎችንና መርሆዎችን፡ እንዲሁም የሀገራትን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ሊያከብሩ እንደሚገባ የሚያትት ነው።
ሦስተኛው፡ ግጭቶችን ማቆምና ሰላም መገንባት ሲሆን፡ ተነጥሎ የሚደረግ ማዕቀብና ጦርነት መፍትሔ አለመሆኑን ያስረዳል።
አራተኛው ደግሞ የችግሩን ምልክቶችና መሠረታዊ ምክንያት መለየትና መረዳት የሚል ነው። እነዚህ መርሆዎች ለቀንደ አፍሪካ ችግሮችም አቅጣጫ እንደሚሰጡ ተገልጿል።

