ዐቢይ አሕመድና ኔታንያሁ በስልክ ተነጋገሩ
ንግግሩ የተደረገው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት በተካረረበት ወቅት ነው።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን አስታወቁ።
በንግግሩ ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያና በእስራኤል መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ስለማጠናከርና ስለ ቀጣናዊ ሁኔታዎች በሰፊው መምከራቸው ተገልጿል።
የግንኙነቱ ዋና ትኩረት በቴሌኮም፡ በአቪዬሽን፡ በሎጂስቲክስና በኢነርጂ ዘርፎች ትብብርን ማሳደግ እንደነበር ተነግሯል።
ይህ ንግግር የተደረገው በቅርቡ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዴዎን ጢሞቲዎስና በእስራኤሉ አቻቸው ጊዴዎን ሳዓር መካከል የተደረገውን ተመሳሳይ የስልክ ንግግር ተከትሎ ነው።
