አሜሪካና የአውሮፓ ኅብረት ስለ ኤርትራና ኢትዮጵያ ተወያዩ
ማሳድ ቡሎስና አኔት ዌበር በሱዳን ቀውስና በኤርትራ–ኢትዮጵያ ውጥረት ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

የትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ በአረብና አፍሪካ ጉዳዮች ማሳድ ቡሎስ፣ ከአውሮፓ ኅብረት የቀጠናው ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበር ጋር ተገናኝቶ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ያለመ የጋራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ላይ ጥልቅ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቋል።
ውይይቱ በቅድሚያ እየተወሳሰበ በመጣው የሱዳን ቀውስ ላይ ያተኮረ እንደነበርና እንዲሁም አሁን ጫፍ በደረሰው የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጥረት ላይ መምከራቸውን ቡሎስ በኤክስ ገጹ አስታውቋል።
የአውሮፓ ኅብረት በሱዳን ጉዳይ በአምስት ቡድን በተመሠረተው አካል አባል በመሆኑ፣ የሱዳን ሕዝብ ራሱ ችግሩን የሚፈታበት ሲቪላዊ የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።
ተንታኞች ግንኙነቱ ምዕራባውያን ኃይሎች በቀጠናው ሌላ አውዳሚ ግጭት እንዳይቀሰቀስ የመከላከል ዲፕሎማሲያቸውን መቀጠላቸውን እንደሚያሳይ ይገልጻሉ።
