በአስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የጸጥታ ማስጠንቀቂያ አወጣ
የአሜሪካ ዜጎች የመውጫ ዕቅድ እንዲያዘጋጁና ሰነዶቻቸውን ዝግጁ እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል
በኤርትራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ፡ በሰሜን ኢትዮጵያ በኤርትራ ድንበር አካባቢ ውጊያ መቀጠሉን በመግለጽ፡ በኤርትራ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዓርብ ጥቅምት 9 ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።
ኤምባሲው በመግለጫው፡ ኤርትራ ለድርብ ዜግነት ዕውቅና ስለማትሰጥ፡ የአሜሪካና የኤርትራ ድርብ ዜግነት ላላቸው ሰዎች ሊሰጥ የሚችለው እገዛ ውስን ሊሆን እንደሚችል አብራርቷል።
የኤምባሲው ሠራተኞች ከአስመራ ከተማ ውጪ ከ25 ኪሎ ሜትር በላይ መጓዝ ስለማይችሉ፡ ከዚህ ርቀት ውጪ ለሚንቀሳቀሱ የአሜሪካ ዜጎች የእገዛ አቅም ውስን መሆኑ ተገልጿል።
ኤምባሲው ዜጎች ከአሜሪካ መንግሥት እገዛ ሳይጠብቁ ከኤርትራ የመውጫ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ፡ ወቅታዊ የጉዞ ሰነዶቻቸውን በእጃቸው እንዲይዙና የዜና ማሰራጫዎችን እንዲከታተሉ አሳስቧል።
