ሕወሓት ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ
ወታደራዊ ጭነት ካልቆመ አውሮፕላኖችን በወታደራዊ ዒላማ ውስጥ እንደሚያስገባ ገልጿል።

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፡ የመቐለን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለወታደራዊ አገልግሎት እየተጠቀመ ያለውን የብልጽግና ፓርቲና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ሊመታ እንደሚችል አስጠንቅቋል።
ይህን የገለጸው፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትላልቅ የጭነት አውሮፕላኖችን በመጠቀም የፌዴራል ሠራዊትን ሎጂስቲክና የሰው ኃይል ወደ መቐለ እያጓጓዘ መሆኑ በማስረጃ በተረጋገጠበት ወቅት ነው።
ሕወሓት በመግለጫው፡ ሲቪል አየር መንገድ በትግራይ ሕዝብ ላይ እንደ ዋና መሣሪያ መሆኑ ከዓለም አቀፍ ሕግ ውጪ መሆኑን በማጽናት፡ ድርጊቱ በአጭር ጊዜ ካልቆመ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖችን በወታደራዊ ዒላማዎቹ ውስጥ እንደሚያስገባ አስጠንቅቋል።
ድርጊቱ ግልጽ የዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት መሆኑንና በዓለም አቀፍ መድረኮች ሊመረመር እንደሚገባ ብዙዎች ይስማማሉ።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ይፋዊ ምላሽ አልተሰጠም።
