ሕወሓት አዲሱን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውድቅ አደረገ
ከአስተዳደሩ ጋር የሚተባበሩ ተቋማት ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስጠንቅቋል።

የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አመራር፡ በፌዴራል መንግሥት የታወጀውን አዲሱን የስድስት ወር የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል።
በፌዴራል የተሾመው ጊዜያዊ አስተዳደር በገዢው ፓርቲ የተጫነ ፖለቲካዊ መዋቅር በመሆኑ፡ የሚያስተላልፈው ማንኛውም ውሳኔ ሕጋዊነትም ሆነ ተፈጻሚነት እንደሌለው ገልጿል።
ከአዲሱ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር የሚተባበሩ ተቋማትና ሰዎች የገዢው ፓርቲ ቀጣይ ተደርገው ተጠያቂ እንደሚሆኑም አስጠንቅቋል።
በተጨማሪም፡ የፌዴራል መንግሥት የመቐለን አውሮፕላን ማረፊያ ከሲቪል አገልግሎት ውጪ ሠራዊትና ወታደራዊ አቅርቦቶችን ለማጓጓዝ እየተጠቀመበት ነው ሲል ከሷል።
እርምጃው የመጣው የፌዴራል መንግሥት ትግራይን የሚመሩ አምስት ባለሥልጣናትን ከሾመ በኋላ ነው።
