የትግራይ ኃይሎች በሁለት ቀናት 1,511 የፌዴራል ወታደሮች መግደላቸውን ገለጹ
ሕወሓት በሰሜን ትግራይ በተደረገ ውጊያ 1,050 መቁሰላቸውንም አስታውቋል።

በሕወሓት የሚመራው የትግራይ ኃይሎች፡ በሰሜናዊ የትግራይ ክልል ክፍል ጥቅምት 17 ቅዳሜና ጥቅምት 18 እሁድ ባካሄዱት የሁለት ቀናት ውጊያ፡ 1,511 የፌዴራል ወታደሮች መግደላቸውንና 1,050 ማቁሰላቸውን ገልጸዋል።
ከሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች አንዱ ነጋሽ ሕሉፍ ይህን ቁጥር እንደሰጡ አናድሉ የተባለው የመረጃ ድረ-ገጽ ዘግቧል።
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በመካከለኛው ትግራይ አካባቢ፡ ወደ ዓደት ከተማ ለመግስገስ የሞከረውን የፌዴራል ሠራዊት መግታታቸውንም ተናግረዋል።
ከፌዴራል መንግሥት ጎን ከተሰለፉት የትግራይ ሰላም ኃይል ታጣቂዎች 11 አባላት መግደላቸውንም አክለዋል።
እነዚህ ሪፖርቶች በገለልተኛ አካል አልተረጋገጡም፤ ከፌዴራል መንግሥት በኩልም እስካሁን ይፋዊ ምላሽ አልተሰጠም።

