ሳዑዲ ዓረቢያ ሁለት የባንግላዲሽ ዜጎችን በሞት ቀጣች
በመካ መስጊድ ውስጥ ሥነ ምግባር የጎደለው ድርጊት ፈጽመዋል ተብለው ተከሰው ነበር።

ናዝሩል ኢስላም አብዱል ባሲርና ሲቲ አኽታር የተባሉ ሁለት የባንግላዲሽ ዜጎች፡ በመካ በሚገኘው መስጊድ ውስጥ ሥነ ምግባር የጎደለው ድርጊት ፈጽመዋል ተብለው ከተከሰሱ በኋላ፡ በሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት የሞት ፍርድ ተፈጽሞባቸዋል።
በማኅበራዊ ሚዲያና በባንግላዲሽ የዜና ማዕከላት እንደተገለጸው፡ ክሱ አዲስ ተጋቢዎቹ ለጫጉላ ሽርሽር ወደ መካ በሄዱበት ወቅት፡ ባለቤቱ ሚስቱን ግንባሯ ላይ መሳሙ ጋር የተያያዘ ነው።
ይህ ድርጊት ለጋብቻቸው ለአላህ ያላቸውን ምስጋና መግለጫ እንደነበር ተገልጿል።
አስከሬናቸው በሁለት ሣጥኖች ተገንዞ ወደ ባንግላዲሽ መመለሱ ታውቋል።

