ሩሲያ የኒውክሌር አቅም ያላቸውን አውሮፕላኖች በባልቲክ ባሕር አየር ክልል አበረረች
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር፡ የባሕር ግዛቷን ደህንነት ለማስጠበቅ መሆኑን ገልጿል።

ሩሲያ ጥቅምት 16፡ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ መያዝ የሚችሉ ስትራቴጂያዊ ቦምብ አጥፊ አውሮፕላኖችን በባልቲክ ባሕር አየር ክልል አበረረች።
የእርምጃው ዓላማ የሀገሪቱን የባሕር ግዛት ደህንነት ለማስጠበቅ መሆኑን የገለጸው የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር፡ በዓለም አቀፍ ሕጎች መሠረት መከናወኑንና ሌሎች ሀገራትን በአሉታዊ መልኩ እንደማይጎዳ አስረድቷል።
ሩሲያ ባለፉት ሰኔና ሐምሌ ወራትም በባልቲክ ባሕር አየር ክልል ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎችን ማድረጓን ሪፖርቶች ይጠቅሳሉ።
በባልቲክ ባሕር አየር ክልል ብቻ ሳይሆን፡ በአርክቲክ ውቅያኖስ፡ በአትላንቲክ ውቅያኖስ፡ በፓሲፊክ ውቅያኖስና በጥቁር ባሕርም በረራዎችን ስታደርግ መቆየቷ ይታወቃል።
አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ሀገራትም በእነዚህ የባሕር አካላት ተመሳሳይ በረራዎችን እንደሚያደርጉ ይገለጻል።
