ሪፖርት፡ የብልጽግና ወታደራዊ መዋቅር በውጭ ኃይሎች ይመራል
በዘጠኝ ወራት 365 የጭነት አውሮፕላኖች ወታደራዊ ድጋፍ ወደ አዲስ አበባ መድረሳቸው ተገልጿል።

የብልጽግና ፓርቲ ወታደራዊና የደህንነት መዋቅር ምንም የሀገር ውስጥ መሠረት እንደሌለውና በውጭ ኃይሎች የሚመራ መሆኑን ሪፖርቶች ገልጸዋል።
ሓዳስ ኤርትራ ጋዜጣ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፡ በ2026 የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ብቻ 365 የጭነት አውሮፕላኖች ወታደራዊ ቁሳቁስ በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አርፈዋል።
ዋና ለጋሾቹ የተባበሩት ዓረብ ኤሜሬትስና አዘርባጃንን የሚያካትቱ ሀገራት መሆናቸውን ሪፖርቱ ይገልጻል።
ብልጽግና ባለፉት ስምንት ዓመታት ከበርካታ ለጋሾች በድምሩ ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቱም ተገልጿል።
በአንፃሩ፡ 21.4 ሚሊዮን ያህል የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕልውናው በሰብአዊ እርዳታ ላይ የተመሠረተ ሆኖ ቀጥሏል። እነዚህ ሪፖርቶች በገለልተኛ አካል አልተረጋገጡም።
