በአማራ ክልል ሠራዊቱን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሄደ
በጎንደር፣ በሰቆጣ፣ በደብረ ታቦር፣ በወልድያና በገንዳ ውሃ ሰልፍ ተደርጓል።

በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የመከላከያ ሠራዊቱን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
የድጋፍ ሰልፉ በጎንደር፣ በሰቆጣ፣ በደብረ ታቦር፣ በወልድያ፣ በገንዳ ውሃና በሌሎች ከተሞች እየተካሄደ ይገኛል።
ሰልፈኞቹ፡ የመከላከያ ሠራዊቱ የሀገርን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማጠናከር የሚያደርገውን ትግል ለመደገፍ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በሰልፉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ወጣቶችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት እየተሳተፉ መሆኑ ተነግሯል።
