ጃፓን ወደ ማርስ ጨረቃ ሰው አልባ መንኮራኩር ላከች
በነሐሴ 2027 እንደምትደርስና በ2031 ናሙናዎችን ይዛ እንደምትመለስ ይጠበቃል።

ጃፓን ጥቅምት 20 ወደ ማርስ ጨረቃ ሰው አልባ መንኮራኩር መላኳን አስታውቃለች።
ይህ አዲስ ተልእኮ፡ ከዚህ ቀደም ካልተዳሰሰችው ጨረቃ ለጥናት የሚሆኑ ናሙናዎችን ለማምጣት ያለመ መሆኑን የጃፓን የጠፈር ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
መንኮራኩሯ በነሐሴ 2027 ወደ ማርስ እንደምትደርስ፡ በ2031 ደግሞ ናሙናዎችን ይዛ ወደ ምድር እንደምትመለስ ይጠበቃል።
ተልእኮው በማርስ ፕላኔት ላይ ለሚደረግ ጥናት አጋዥ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይጠቁማሉ።
በተጨማሪም፡ የጠፈር ተልእኮው ጃፓን በጠፈር ዘርፍ ያላትን ምኞት ወደፊት የሚገፋ መሆኑ ተጠቅሷል።

