ሑቲ በዓደን የሚገኘውን የየመን ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ደበደበ
አምስት ሰዎች ሲገደሉ 16 ቆስለዋል።

የየመን ታጣቂ ቡድን ሑቲ፡ በዓደን ከተማ በሚገኘው የየመን ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ሕንፃ ላይ የሚሳይል ጥቃት ማካሄዱ ተገልጿል።
አምስት ሰዎች ሲገደሉ 16 ሰዎች መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
ሑቲ አል ማሻቅ በሚል የሚታወቀውን የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት በአምስት ባላስቲክ ሚሳይሎች መደብደቡን፡ በጥቃቱ ወቅትም የየመን ጠቅላይ ሚኒስትርና ሌሎች የካቢኔ አባላት በጽሕፈት ቤቱ ግቢ ውስጥ እንደነበሩ ተነግሯል።
የየመን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻያ አል ዚዳኒ ድብደባውን በማውገዝ፡ በሑቲ ላይ እየተደረገ ያለው ወታደራዊ ዘመቻ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ሑቲ ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በሪያድ ንጉሥ ካሊድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጥቃት ካደረሰ በኋላ 14 ሰዎችን ገድሎ ከ300 በላይ አቁስሏል።
