ኤርትራ በአሰብ ዛቻ ላይ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈች
የኤርትራ ትዕግስት የሚያልቅበት ጊዜ መቃረቡን በመግለጫዋ ገልጻለች።

ኤርትራ በኢትዮጵያ መንግሥት እየቀረበ ያለውን ትምክህትና የአሰብን መቀላቀል ፈጽሞ እንደማትቀበለው በመግለጽ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ አስተላልፋለች።
የኢትዮጵያ ኃይሎች በኤርትራ ድንበር የሚያደርጉት እንቅስቃሴና ስለ አሰብ ወደብ የሚቀርበው ተደጋጋሚ የወረራ ዛቻ ካልቆመ፡ ኤርትራ ሉዓላዊነቷን ለመከላከል የማያዳግም እርምጃ እንደምትወስድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
ኤርትራ ጦርነት እንደማትፈልግ ብትገልጽም፡ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እያደረገ ያለው ስትራቴጂያዊ የስሌት ስህተት ወደ ከባድ መዘዝ እንደሚመራ አስታውቃለች።
ኤርትራ ከኢትዮጵያ፡ ከሱዳን ወይም ከጅቡቲ መሬት አንዲት ስንዝር እንደማትፈልግ፤ በተመሳሳይም ከሉዓላዊ መሬቷ አንዲት ስንዝር ለማንም አሳልፋ እንደማትሰጥ አስረድታለች።
ይህን ሁሉ ትምክህት ለረጅም ጊዜ በትዕግስት ለማለፍ ብትሞክርም፡ ትዕግስቱ የሚያልቅበት ጊዜ መቃረቡንና የኤርትራ ዝምታ እንደ ፍርሃት ሊተረጎም እንደማይገባ መግለጫው ያስጠነቅቃል።
