ኤርትራ በናይሮቢ የንግድና የኢንቨስትመንት ጉባኤ ተሳተፈች
ከ50 በላይ ሀገራትን የወከሉ ከ5 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ኤርትራ በናይሮቢ ኬንያ በአፍሪካ አዲስ የንግድ ዘመንን መምራት በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው የንግድና የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ ተሳትፋለች።
በጉባኤው ከ50 በላይ ሀገራትን የወከሉ አምራቾች፡ አቅራቢዎች፡ ባለሀብቶችና የንግድ ተቋማት ተወካዮችን ጨምሮ ከ5 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
የጉባኤው ዋና ጭብጦች ንግድ፡ ኢንቨስትመንት፡ ፈጠራ፡ አመራርና ትስስር እንደነበሩ ተገልጿል።
ጉባኤው በደህንነት፡ በባሕር አካላት ሉዓላዊነትና በሰላም፡ በሴቶችና በወጣቶች ተጠቃሚነት ላይ ያተኮሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች፡ እንዲሁም በኢንዱስትሪ ሉዓላዊነት ላይ ያተኮረ እንደነበር ተነግሯል።
በሀገራት መካከል የሚደረገውን የንግድ እንቅስቃሴ ለማሳደግና የአፍሪካን ሰላም ለማረጋገጥ በተቀናጀ መንገድ መሥራት እንደሚያስፈልግ በጉባኤው ተወያይቷል።
