በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ሕጋዊ ጥያቄ አስነሱ
በትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎችና ንጹሐን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ከባድ የሕጋዊነትና የሥነ ምግባር ጥያቄ እያስነሳ መሆኑ ተገልጿል።

በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየጨመረ የመጣው ግጭት፣ ጅምላ ግድያና የሰብአዊ መብት ጥሰት ከባድ የሕጋዊነትና የሥነ ምግባር ጥያቄዎች እያስነሳ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ዓይነት ጥቃት በአርሲ፣ በወለጋና በቦረና በተደጋጋሚ ሲካሄድ መቆየቱን፣ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያንና መነኮሳት ሳይቀሩ ተጠቂ መሆናቸውን ሪፖርቶች ያስረዳሉ።
ከእጅግ አስደንጋጭ ከተባሉት ክስተቶች መካከል በደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ ጥቅምት 10 በመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት ይጠቀሳል።
የድሮን ጥቃቶች በአማራ ክልል በትምህርት ቤቶች፣ በሆስፒታሎችና በመሠረተ ልማቶች ላይ ከሚፈጸሙ ሦስት ዓመታት እንደቆጠሩ የገለጹት ሪፖርቶች፣ የአገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ምንም መግለጫ አለመስጠቱን ተችተዋል።
