በአስመራ የሚገኙ ዲፕሎማቶች በኢትዮ-ኤርትራ ውጥረት ላይ አስተያየት ሰጡ
በኤርትራ ሉዓላዊ ክብር ላይ ትንሽም ጥሰት እንደማይፈቀድ ገልጸዋል።

በአስመራ የሚገኙ የበርካታ ሀገራት ተወካዮች፡ በቀንደ አፍሪካ ቀጣና ተጨማሪ ግጭት መቀስቀስ ለዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ግልጽ ስጋት መሆኑን ገልጸዋል።
የአሜሪካ፡ የታላቋ ብሪታንያ፡ የፈረንሳይና የሌሎች የአውሮፓ አባል ሀገራት ተወካዮች፡ እንዲሁም የአፍሪካ አህጉርና የቀንደ አፍሪካ ቀጣና ተወካዮች በመግለጫቸው፡ ሉዓላዊነትና ሀገራዊ አንድነት የዓለም አቀፍ ግንኙነቶች የማዕዘን ድንጋይ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በአንዲት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አባል ላይ የሚደረግ ጥሰት፡ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት በሁሉም አባል ሀገራት ላይ ጫና የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸዋል።
ተወካዮቹ ይህን አስተያየት የሰጡት፡ ከኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በቀንደ አፍሪካ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ባደረጉት ግንኙነት ነው።
ሚኒስትር ዑስማን ሳልሕ ጥቅምት 15 ለዲፕሎማሲያዊ ማኅበረሰቡ አባላት፡ በኤርትራ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ላይ ስለሚፈጸመው ጥሰትና በቀጣናው ሰላም ላይ ስላለው ተፅዕኖ ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል።
