በሳዑዲ ዓረቢያ የነበሩ 1,447 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
ከተመላሾቹ 1,139 ወንዶች፡ 261 ሴቶችና 47 ሕፃናት ናቸው።

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1,447 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ከተመላሾቹ 1,139 ወንዶች፡ 261 ሴቶችና 47 ሕፃናት ሲሆኑ፡ ከእነርሱም 47ቱ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።
ለተመላሾቹ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በመቀበያ ማዕከላት ተገቢው ድጋፍ እየተደረገላቸው ከቤተሰቦቻቸው የማገናኘት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
