ሕወሓት የመቐለን አየር ማረፊያ ተቆጣጠረ፤ በረራዎች ቆሙ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ፣ አክሱምና ሽረ የሚያደርጋቸውን በረራዎች ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጧል።

የትግራይ ኃይሎች የአሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያን መቆጣጠራቸው ተገልጿል። ርክክቡ ያለ ምንም የተኩስ ልውውጥ መፈጸሙና በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ፣ ከመስከረም 23 ጀምሮ ወደ መቐለ፣ አክሱምና ሽረ ከተሞች ያደርጋቸው የነበሩትን በረራዎች ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡን በይፋ አስታውቋል።
አየር መንገዱ በመግለጫው ምንም ምክንያት ሳይጠቅስ፣ ለደንበኞቹ ለሚፈጠሩ መስተጓጎሎች ይቅርታ መጠየቁን ብቻ ገልጿል።
በመቐለ ከተማ የሚገኙና በፌደራል ፖሊስ አባላት ይጠበቁ የነበሩ የፌደራል መንግሥት ተቋማትም ለትግራይ ኃይሎች መረከባቸው ተገልጿል።

