የትግራይ ኃይሎች ሓገረ ሰላም ከተማን መቆጣጠራቸውን አስታወቁ
ከመቐለ 40 ኪሎ ሜትር ያህል በሰሜን ምዕራብ የምትገኝ ከተማ ናት።

የትግራይ መከላከያ ኃይሎች ሓገረ ሰላም ከተማን በቁጥጥራቸው ሥር ማስገባታቸውን አስታውቀዋል። ከተማዋ ከመቐለ 40 ኪሎ ሜትር ያህል በሰሜን ምዕራብ ትገኛለች።
በሌላ በኩል፡ የዓይን እማኞች እንደገለጹት የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት ከራማ ወደ ዓድዋ እየተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ሠራዊት ራማንና ዛላምበሳን ጨምሮ ከድንበር አካባቢዎች ወደኋላ እየተሰበሰበ መሆኑና የተረፈውን ኃይል በሽረ፡ ሸራሮ፡ አክሱም፡ ዓድዋና ዓዲግራት እያከማቸ መሆኑ ተነግሯል።
በሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሚገኙት ማእከል ዛናና ደደቢት አስቀድመው በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መግባታቸው ይነገራል።
ሁለቱም ሪፖርቶች በገለልተኛ አካል አልተረጋገጡም።
