ዑስማን ሳልሕ ከሱዳንና ከኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተገናኘ
የሁለትዮሽ ግንኙነቶችንና የቀጣናውን ጉዳዮች ያካተተ ውይይት ቅዳሜ 26 መስከረም በኒውዮርክ ተካሂዷል።

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳልሕ፣ ከተለያዩ አቻዎቹ ጋር እያደረገ ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ቅዳሜ 26 መስከረምም ቀጥሏል።
ከሱዳን ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይና የዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ሞሂ-ኤልዲን ሳሌም ጋር በነበረው ውይይት፣ በኤርትራና በሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም የጋራ ጥቅም ባላቸው የቀጣና ጉዳዮች ላይ ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጡን፣ የኤርትራ በተባበሩት መንግሥታት የተወካይ ጽሕፈት ቤት ገልጿል።
በዚያው ቀን ደግሞ ከኦማን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰይድ በድር ጋር፣ በሁለቱ እኅትማማች አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የታለመ ውይይት አድርጓል።
ውይይቱ የጋራ ስጋት ያላቸውን የተለያዩ የቀጣናና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ያካተተ እንደነበር ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል።

