ማዕቀቡ መነሳቱ በኢንቨስትመንትና ንግድ አዲስ ምዕራፍ ሊከፍት ይችላል
ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል፣ እርምጃው የሁለቱ አገራት የተጠራቀመ ቅን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል፣ አሜሪካ ኤርትራን የሚመለከተውን ማዕቀብ ለማንሳት የወሰደችውን ውሳኔ በደስታ እንደሚቀበሉት ገልጸዋል።
እርምጃውን፣ የሁለቱም አገራት ገንቢ የሆነ የፖለቲካ ቅን ፍላጎት የተጠራቀመ ውጤት የሚያንጸባርቅ መሆኑንና በሁለትዮሽ ትብብር በተለይም በኢንቨስትመንትና በንግድ አዲስ ምዕራፍ ሊከፍት እንደሚችል አስረድተዋል።
ሚኒስትር የማነ ይህን የገለጹት ከአሽ-ሸርቅ አል-አውሳጥ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለ መጠይቅ ሲሆን፣ ማዕቀቡ ከመጀመሪያውም በማንኛውም መመዘኛ ምክንያታዊ አልነበረም ሲሉ ገልጸዋል።
ኤርትራ በተለያዩ ዘርፎች ብልጫዎች እንዳሏትና ቀድመው በተመሠረቱ ሕጋዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮች ተደግፋ ለኢንቨስትመንት በሯ ክፍት መሆኑን ተናግረዋል።

