ኤርትራና የተባበሩት መንግሥታት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ትብብራቸውን ያጠናክራሉ
የተባበሩት መንግሥታት በሰው ሠራሽ አስተውሎትና በልማት ትርክት ከኤርትራ ጋር እየሠራ ነው።

በተባበሩት መንግሥታት ቀን ምክንያት በተዘጋጀው፡ ሰው ሠራሽ አስተውሎትና የኤርትራ የልማት ትርክት በሚል ጭብጥ በተካሄደ የውይይት መድረክ፡ በኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት አስተባባሪ ሚስ ናህላ ቫልጂ መግለጫ ሰጥተዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ከኤርትራ መንግሥት የልማት ቅድሚያዎች ጋር በማስተሳሰር፡ ሰፊ የቴክኖሎጂ ድጋፎችን ለማድረግ መነሳሳቱን ገልጸዋል።
ሚስ ናህላ በመግለጫቸው፡ ሰው ሠራሽ አስተውሎት አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ፡ በሰብአዊ ክብር፡ በሀገራዊ ቅድሚያዎችና በውስጣዊ እውነታ ላይ የተመሠረተ ከሆነ የልማት ሂደትን እንደሚያፋጥን ተናግረዋል።
በመድረኩ አቅም መገንባት፡ ተደራሽነትን ማጠናከርና የወደፊቱን መቅረጽ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በኤርትራና በተባበሩት መንግሥታት መካከል በአቅም ግንባታ፡ በጤናና በትምህርት ሰፊ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑም ተገልጿል።
