ኤርትራ በአብይ አሕመድ የኖቤል ሽልማት ላይ ቅሬታዋን ገለጸች
የሰላም ተሸላሚው በጦርነትና በጥፋት የሚወዳደረው እንደሌለ በወጣ ትንታኔ ተገልጿል።

አልፍሬድ ኖቤል ከፈጠራው ያገኘውን ሀብት፡ ሰላም ለሚፈጥሩ ሽልማት እንዲሰጥበት ማዕከል ማቋቋሙ ይታወሳል።
በ2018 በኢትዮጵያ ሥርዓት ሲቀየር፡ የቀንደ አፍሪካ ችግር ያበቃል የሚል ተስፋ ታየ። አዲሱ መሪ ወደ አስመራ በርሮ የሰላምና የወዳጅነት ስምምነት ሲፈርም፡ ዓለም ሳታወላውል የኖቤል የሰላም ሽልማት ሰጠችው።
እውነተኛ ባሕርይውን ለማጋለጥ ግን ጊዜ አልወሰደም። በሥልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው የማታውቅ ግጭትና የእርስ በርስ ጦርነት አስተናገደች።
የመቶ ሺዎች ኢትዮጵያውያን ሕይወት ጠፋ፤ 12 ሺህ ትምህርት ቤቶች ወድመውና ተዘግተው ከ8 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ከትምህርት ተነፈጉ፤ ከ21 ሚሊዮን በላይ ሕዝብም የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ጠባቂ ሆነ።
የጎረቤት ሱዳንን ሰላም ማወክና በባሕር በር ሰበብ በኤርትራ ላይ የሚደረግ ዛቻም ተጨመረበት። በጦርነትና በጥፋት የኖቤል ሽልማት ቢኖር የሚወዳደረው አይገኝም ሲል ትንታኔው ይደመድማል።

