የኮሉሊ ፖታሽ ፕሮጀክት በገበያው ፊት ለፊት ተሰለፈ
1.1 ቢሊዮን ቶን ክምችት፤ የመጀመሪያው የንግድ ምርት በ2027 መጨረሻ ላይ ይጠበቃል።

በኤርትራ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት የኮሉሊ ፖታሽ ፕሮጀክት በዚህ ዓመትም እድገቱን መቀጠሉና በዓለም የፖታሽ ገበያ ላይ እንደ ዋና ተዋናይ ከፊት ተሰልፎ መሆኑ ተገለጸ።
አሜሪካዊው የመረጃ ድረ ገጽ ተንደርጎ በሰጠው ማብራሪያ፣ ፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳ ችግሮች አጋጥመውት የነበረ ቢሆንም፣ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታውና የሀብት መሠረቱ ስፋት ግን አልቀነሰም ሲል ገልጿል።
ፕሮጀክቱ ከዓለም አቀፍ አቅራቢዎች፣ ከኮንትራክተሮችና በኤርትራ የማዕድን ዘርፍ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ከሚፈልጉ ባለሀብቶች ከፍተኛ ትኩረት እየሳበ መሆኑን አስረድቷል።
የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲጠናቀቅ በዓመት 472,000 ቶን ፖታሺየም ሰልፌት እንደሚያመርት፣ በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ወደ 944,000 ቶን እንደሚያድግ ተገልጿል።
የፖታሺየም ሰልፌት ማዕድን ለእርሻ ምርት ወሳኝ በመሆኑ፣ ይህ የኤርትራ ፕሮጀክት በዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ጥረቶች ላይ ዋና አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

