የሕፃናት ክትባት ወደ ኤርትራ ገባ
ከጋቪ የክትባት ኅብረትና ከዩኒሴፍ ጋር ባለው ትብብር፣ 95 በመቶ የክትባት ሽፋንን ለማስቀጠል።

የኤርትራ መንግሥት ከጋቪ የክትባት ኅብረትና ከዩኒሴፍ ጋር ባለው ቀጣይ ትብብር አዲስ የሕፃናት ክትባት ወደ ኤርትራ መግባቱን በኤርትራ የሚገኘው የዩኒሴፍ ጽሕፈት ቤት ገልጿል።
ይህ ትብብር 95 በመቶ የክትባት ሽፋን እንዲቀጥልና በመላው አገሪቱ የሚገኙ ሕፃናትን በክትባት መከላከል ከሚቻሉ በሕይወታቸው ላይ አደጋ ከሚያስከትሉ በሽታዎች ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል።
ክትባቱ የኤርትራ መንግሥት በጤና ሚኒስቴር በኩል የሚያካሂደውን አገራዊ የክትባት ዘመቻ አጅቦ የሚሄድ ነው።

