የተባበሩት መንግሥታት በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ስጋቱን ገለጸ
እስቴፋን ዱጃሪክ፡ ወታደራዊ እርምጃ የፖለቲካ ልዩነቶችን አይፈታም።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ በኢትዮጵያ በታጣቂ ቡድኖች መካከል በተፈጠረው አዲስ ጥምረት፣ በቀጠለው የጸጥታ ችግርና በድሮን ጥቃቶች ላይ ያለውን ስጋት አስታውቋል።
የዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ እስቴፋን ዱጃሪክ በዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸው፣ ከፍተኛ ውጥረት በሚታይበት በዚህ ወቅት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን ይበልጥ ሊያባብሱ ከሚችሉ ተግባራት ወይም መግለጫዎች እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ወታደራዊ እርምጃ የፖለቲካ ልዩነቶችን የሚፈታ አይደለም በማለት፣ መሠረታዊ ቅሬታዎችንም አይመልስም ሲሉ ገልጸዋል።
ቃል አቀባዩ በመጨረሻም፣ ድርጅቶቹ ለውይይት የታደሰ ተነሳሽነት እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።

