የአሜሪካ ማዕቀብ መነሳት በኤርትራ የማዕድን ዘርፍ አወንታዊ ውጤት እንዳለው ተገለጸ
የዳናካሊ ሥራ አስፈጻሚ ሊቀ መንበር ሲሙስ፡ እርምጃው ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የሚጠበቅ አወንታዊ እድገት መሆኑን ገለጸ።

በኤርትራ ላይ የተጣለው የአሜሪካ ማዕቀብ መነሳት፡ በማዕድን ዘርፍ ላይ አወንታዊ ውጤት እንዳለው ተገልጿል።
በኤርትራ ቀደም ሲል በኮሉሊ ፖታሽ ፕሮጀክት 50 በመቶ ድርሻ የነበረውና በኋላም ለቻይናው ኩባንያ SRBG በ121 ሚሊዮን ዶላር የሸጠው ዳናካሊ የተባለው ኩባንያ፡ ሥራ አስፈጻሚ ሊቀ መንበሩ ሲሙስ ስለ ማዕቀቡ መነሳትና በዘርፉ ላይ ስላለው ተጽዕኖ አስተያየቱን ሰጥቷል።
እሱ፡ ይህ ለኤርትራና ለብዙ ኤርትራውያን ወዳጆቻችን አወንታዊና ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የሚጠበቅ እድገት ነው፡ ምክንያቱም በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ያጋጥማቸው የነበረውን ከባድና ተገቢ ያልሆነ እንቅፋት ስለሚያስወግድ ሲል ገልጿል።
በአውስትራሊያ መቀመጫውን ያደረገው የፍለጋና የልማት ኩባንያ ዳናካሊ፡ በኤርትራ የነበረውን ስትራቴጂ ከፖታሽ ማዕድን ወደ ውድና መሠረታዊ ማዕድናት በማሸጋገር፡ በአስመራ አካባቢ እየሠራ ነው። ኩባንያው፡ በዚህ ልማትን በሚያፋጥን ክስተት፡ በማዕድናት ልማትና ፍለጋ ላይ የነበረውን ረጅም ተሳትፎ ለመቀጠል በጉጉት እየጠበቀ መሆኑ ተገልጿል።
ይህን መግለጫ፡ በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር አቶ እስቲፋኖስ መስከረም 23 ባወጡት አጭር የማኅበራዊ ሚዲያ መልእክት አቅርበዋል።
ዳናካሊ፡ እጅግ ተስፋ ባለው የጋሽ ባርካ ዞን፡ ከአስመራ በደቡብ ምዕራብ በሚገኘው የኤላ ገደል የወርቅ ፕሮጀክትና በመሠረታዊ ማዕድናት ላይ አተኩሮ እየሠራ መሆኑን በይፋዊ ድረ ገጹ ይገልጻል።
