ዑስማን ሳልሕ በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ተከታታይ ግንኙነቶችንና መግለጫዎችን አደረጉ
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከአልጄሪያ፡ ከቡርኪና ፋሶና ከግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፡ እንዲሁም ከተባበሩት መንግሥታትና ከብሪታንያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተዋል።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳልሕ ከመስከረም 23 እስከ 25 በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ተከታታይ ውይይቶችን አካሂደዋል። ከአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ ዓጣፍ ጋር ስለ አፍሪካ ሰላምና ደኅንነት፡ የቀይ ባሕርና የአደን ባሕረ ሰላጤ ደኅንነትን ጨምሮ ተወያይተዋል። ከቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካራሞኮ ዣን ትራዖሬ ጋር ደግሞ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማስፋት ተስማምተዋል። ከግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድር ዓብደላጢ ጋር ስለ ሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር ሐሳብ ተለዋውጠዋል። በተጨማሪም ለፖለቲካና ሰላም ግንባታ ጉዳዮች የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ዋና ጸሐፊ ከሆኑት ሮዝመሪ ዲካርሎ እና ከብሪታንያ ብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ጆናታን ፓወል ጋር ስለ ቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ተነጋግረዋል። ማስታወቂያ ሚኒስቴር፡ ከሱዳን፡ ከስዊድንና ከግሪክ ባለሥልጣናት ጋርም ግንኙነቶች መደረጋቸውን ጠቅሶ፡ ዝርዝሩን ግን አላስቀመጠም። በተመሳሳይ ጊዜ ዑስማን ሳልሕ በ50ኛው የቡድን 77 እና ቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዓመታዊ ስብሰባ፡ ወረርሽኝን በመከላከል፡ በመዘጋጀትና ምላሽ በመስጠት ላይ በተካሄደው ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ፡ እንዲሁም የባሕር ወለል ከፍታ መጨመር ስለሚያስከትለው አደጋ በተካሄደው ጉባኤ ላይ መግለጫዎችን አቅርበዋል። ምንጭ፦ ሻዕቢያ / የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር።
