ዑስማን ሳልሕ ለጎረቤት አገር ስለ ቀይ ባሕር ግልጽ መልእክት አስተላለፈ
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ስብሰባ ላይ የባሕር ወለል መጨመርን አስመልክቶ ባደረገው ንግግር፣ የባሕር ዳርቻ አገሮች ሉዓላዊ መብቶች እንዲከበሩ አጽንኦት ሰጥቷል።

በኒውዮርክ የኤርትራን ልዑክ መርቶ በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ የሚገኘው የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ዑስማን ሳልሕ፣ ሐሙስ 24 መስከረም በተባበሩት መንግሥታት ዋና ጽሕፈት ቤት፣ የባሕር ወለል ከፍታ መጨመር በአገሮች ሕልውና ላይ የሚያስከትለውን አደጋ በሚመለከት በተደረገ ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርጓል።
በንግግሩ፣ ለጎረቤት አገር ኢትዮጵያ ስሟን ሳይጠቅስ ግልጽ መልእክት ማስተላለፉ ተገልጿል።
ኤርትራ የባሕር ወለል መጨመር የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመከላከልና ለመጠበቅ የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰዷን የገለጸው ሚኒስትር ዑስማን፣ የተረጋጉና አስተማማኝ የባሕር ቀጣናዎች እንዲሁም የባሕር ዳርቻ አገሮች በሕጋዊ ውሃዎቻቸው ላይ ያላቸው ሉዓላዊ መብቶች አስፈላጊ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥቷል።
በመጨረሻም፣ የባሕር ዳርቻ አገሮች ዘላቂና የተረጋጋ የባሕር ሥነ-ሕይወት በማረጋገጥና በማጠናከር ረገድ ጠቃሚና አማራጭ የሌለው ሚና እንዳላቸው አብራርቷል።

