ዑስማን ሳልሕ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተገናኘ
ውይይቱ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር መርሆችን፣ የሱዳንን ጉዳይ፣ የቀይ ባሕር ደኅንነትንና የብልጽግና ፓርቲ የማወክ ተግባራትን አንስቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ዑስማን ሳልሕ የኤርትራን ልዑክ መርቶ በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ በመሳተፍ ላይ በሚገኝበት ወቅት፣ ረቡዕ 23 መስከረም ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተገናኝቶ፣ በጠቃሚ የቀጣናና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል።
ሚኒስትር ዑስማን፣ ድርጅቱ ከኤርትራ ጋር ላለው ገንቢ ተሳስሮ ለሚያደርገው አስተዋጽኦ፣ የኤርትራ መንግሥት አድናቆቱን አስተላልፏል።
ሉዓላዊ እኩልነት፣ የግዛት አንድነት፣ የፖለቲካ ነፃነት፣ ጣልቃ አለመግባትና አለመግባባቶችን በሰላም መፍታት የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር መሠረታዊ ምሰሶዎች መሆናቸውን ከጠቀሰ በኋላ፣ የኤርትራን አቋም በሱዳን አንድነትና መረጋጋት ጉዳይ ላይ ለዋና ጸሐፊው አብራርቷል።
በቀይ ባሕርና በባብኤልመንደብ ደኅንነት ጉዳይ ተፈጥሮ ባለው ሁኔታ ላይ ደግሞ፣ በቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኙ አገሮችን ሉዓላዊነትና ሕጋዊ ጥቅሞች የሚያከብር፣ ኤርትራ ለአስተማማኝ የባሕር ጉዞና ለዓለም አቀፍ ትብብር የምታደርገውን ድጋፍ አጽንኦት ሰጥቷል።
ግንኙነቱ፣ የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር መሠረታዊ መርሆችንና የዓለም አቀፍ ሕግን በሚጥስ መልኩ የብልጽግና ፓርቲ በጎረቤቶቹ ላይ ስለሚያደርገው የማወክ ተግባር የሚመለከት ጠቃሚ ውይይትንም አካቷል።
ኤርትራ፣ ከ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ምክትል ፕሬዝዳንቶች አንዷ ሆና ተመርጣለች። በዚህ መሠረት፣ የኤርትራ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ሶፊያ ተስፋማርያም፣ በ8 መስከረም የተደረገውን የመክፈቻ ስብሰባ መርተዋል።
ሚኒስትር ዑስማን፣ ከዓመታዊው ጉባኤ ጎን ለጎን ዲፕሎማሲያዊ ተግባራትን እያደረገ መሆኑ ተገልጿል። ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ማልመር ስቴነርጋርድ ጋር በነበረው ግንኙነት፣ በሁለትዮሽ ጉዳዮችና የጋራ ስጋት ባላቸው የቀጣናና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ውይይት አድርገዋል።

